Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለሀብቶች በቅንጅት በመሥራት የክልሉን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የሚገኙ ባለሀብቶች ተደምረውና ተቀናጅተው በመሥራት የክልሉን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዎላይታ ዞን ቦዶቲ ከተማ ከ100 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ በግል ባለሃብት የተገነባውን የሳሙና እና ቅባት ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ፋብሪካው ተኪ ምርቶችን ማምረት እንዲችል የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ፋብሪካው የምርምርና ሥርፀት ማዕከል በማደራጀት በክልሉ የሚመረቱ ግብዓቶችን በመረከብ መሥራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ በኩል ለኢንቨስትመንት መሬት ወስደው አጥረው ያስቀመጡ ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ የማይገቡ ከሆነ ሕጋዊ ርምጃ ይወሰዳል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version