አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ፡፡
15 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሃዲዱ ብረት ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች መቆራረጣቸውም ተገልጿል፡፡
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የጉዳት መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተፈጠረውን መጠነኛ ጉዳት በፍጥነት በማስተካከል መስመሩን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡