አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተዳደር ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን መገምገም ጀምሯል።
ምክር ቤቱ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት ሦስት ወራት የዕቅዶችን አፈጻጸም በመገምገም ጥንካሬዎችን ፣ ውስንነቶችን እና ትምህርት የሚወሰድባቸው ጉዳዮችን እንደሚለይ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የሁሉም ሴክተሮች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ተግባሩ የተመራበት መንገድና የተገኙ ውጤቶች ተለይተው ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡