የሀገር ውስጥ ዜና

እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ባህር ዳርን ወደተሻለ የከተማነት ደረጃ የሚያሸጋግሩ ናቸው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By Shambel Mihret

October 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ባህር ዳርን ወደተሻለ የከተማነት ደረጃ የሚያሸጋግሩ እና የነዋሪዎችን ህይወት የሚያሻሽሉ ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራ ትስስር ገጻቸው÷ ብርቱ እጆች፣ የማይዝሉ ክንዶች እና የሚያሰላስሉ አዕምሮዎች የዕድገት አየር የሚነፍስባቸውን ከተሞች ይገነባሉ ብለዋል፡፡

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችንና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸው፤ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ባህር ዳርን ወደተሻለ የከተማነት ደረጃ የሚያሸጋግሩ እና የነዋሪዎችን ህይወት የሚያሻሽሉ ናቸው ብለዋል፡፡