አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሩሲያ ፓርላማ በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀረበውን የህገ መንግስት ማሻሻያ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ።
የህ መንግስት ማሻሻያው የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ቆይታ ለማራዘም ይረዳል ተብሏል።
ምክር ቤቱ የህገ መንግስት ማሻሻያውን ያጸደቀው 77 ነጥብ 1 በሆነ አብላጫ ድምጽ መሆኑ ታውቋል።
በዚህ ማሻሻያ መሰረት በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለቀጣይ ሁለት ዙር በፕሬዚዳንትነት መወዳደር ይችላሉ ነው የተባለው።
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ የህገ መንግስት ማሻሻያውን ተቃውመውታል።
ፓርቲዎቹ መቼም ቢሆን ለህገ መንግስት ማሻሻያው እውቅና እንደማይሰጡም አስታውቀዋል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪቭ ፔስኮቭ በበኩላቸው በህገ መንግስት ማሻሻያው ላይ ድል ተቀናጅተናል ሲሉ ተደምጠዋል።