Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሐረር የተገነባው የጅብ ትርዒት ማሳያ ኢኮፓርክ የቱሪዝም አቅምን የሚያጎለብት ነው- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ የተገነባው የጅብ ትርዒት ማሳያ ኢኮ ፓርክ የቱሪዝም አቅም የሚያጎለብት ነው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሯ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጋር በመሆን ነው በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የኢኮ ፓርክ፣ የአርሶ አደር ምርት መሸጫ ማዕከል፣ የአረንጓዴ ልማት እና ሌሎች በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)÷ የቱሪዝም መዳረሻ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ በሆነችው ሐረር ከተማ የተገነባው የጅብ ትርዒት ማሳያ የኢኮ ፓርክ የክልሉን የቱሪዝም አቅም የሚያጎለብት ነውም ብለዋል፡፡

በክልሉ እየተገነባ የሚገኘው የአርሶ አደር ምርት መሸጫ ማዕከልም አምራቹን ከሸማቹ ጋር በማገናኘት ማህበረሰቡ የፈለገውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል።

በክልሉ የተገነባው የአርሶ አደር ምርት መሸጫ ማዕከልም የቅዳሜ ገበያውን ከመንገዶች ላይ በማንሳት በተደራጀ ሁኔታ ለማከናውን እንደሚያስችል መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version