Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ጥላሁን ከበደ በዳራማሎ ወረዳ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎቸን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝታቸውም የሉና ኤክስፖርት ቄራ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተቀናጀ እርሻን እና ሌሎቸ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

ድርጅቱ በ447 ሔክታር መሬት ላይ የአትክልት፣ ቋሚ ተክል፣ የእንስሳት መኖ፣ የከብት ማደለብና የተቀናጀ የግብርና ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ የሥራ ዘርፎቸ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለሀገር ልማት የበኩሉን እየተወጣ መሆኑንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version