አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 የአፍሪካ የአዋቂዎች ጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና የመክፈቻ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመርሐ ግብሩ የባህል ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የአፍሪካ ጤረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ካሊድ አልሳይ እና የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ብዛኔ ተገኝተዋል፡፡
የመከፍቻ መርሐ ግበሩ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በሻምፒዮናው አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ሴኔጋል፣ አንጎላ፣ ቤኒን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩዋንዳ፣ ቶጎ፣ ካሜሮን፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ይሳተፋሉ፡፡