ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

By Mikias Ayele

October 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ምሽት 1 ሰዓት ላይ በአቢጃን ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ለዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ኮትዲቯር አቢጃን የተጓዘ ሲሆን÷ለዛሬው ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

በጨዋታው አማካዩ ቢኒያም በላይ በጉዳት ከመጨረሻዎቹ ልምምድ ውጭ መሆኑ ሲገለጽ ÷ሌሎች ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡