አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕርዳር ከተማ የተገነቡ መናፈሻዎችንና ግዙፉን የአባይ ድልድይ ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷”በውቢቷ ባህር ዳር የተገነቡ መናፈሻዎችን እንዲሁም ግዙፉንና አስደማሚውን የአባይ ድልድይ ጎብኝተናል” ብለዋል።
እነዚህ የልማት ሥራዎች እጅግ ውብ እና ማራኪ ናቸው፤ ለህዝባችን፣ ከሩቅም ከቅርብም ለሚመጡ ቱሪስቶች ማረፊያና መዝናኛነት ምቹ የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት እየሰራን መሆኑን ማረጋገጫ አሻራዎች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።