አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል የወጠነው አዲስ ፈጥኖ ደራሽ የማሽላ ምርት ትልቅ ተስፋ አሳይቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የሐረሪ ክልል የወጠነው አዲስ ፈጥኖ ደራሽ የማሽላ ምርት ትልቅ ተስፋ አሳይቷል ብለዋል፡፡
በክልሉ ከዚህ ቀደም ጾም ያደረ መሬትን በማልማት በሔክታር በአማካይ 43 ኩንታል ምርት ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡