ፋና ማጣሪያ

ሐሰተኛ መረጃ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሃላፊነት ተነሱ የሚል ሐሰተኛ መረጃ በመሰራጨት ላይ ይገኛል

By Melaku Gedif

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሃላፊነት ተነሱ የሚል ሐሰተኛ መረጃ በመሰራጨት ላይ ይገኛል።

ሆኖም ይህ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መደበኛ ስራቸውን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ፋና ማጣሪያ አረጋግጧል።