የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አህመድ ሺዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ሚኒስትር ከሃይበሪው ሎርድ ኮሊንስ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት አቶ አህመድ መንግስት እየተገበረ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ማሻሻያውን ውጤታማ ለማድረግ ዘላቂ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮችን አብራርተዋል።

ሎርድ ኮሊንስ በበኩላቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈጻጸምን ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

የመጣውን ውጤትና የተፈጠረውን የቢዝነስ ከባቢ በማበረታታት፤ ሀገራቸው የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።