አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት ዋና ሊቀመንበር ቶኒ ብሌር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም መጠነ ርዕይ ባላቸው ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት በኢትዮዽያ እያደረገ ባለው ድጋፍ ዙሪያ መምከራቸውንም ጠ/ ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡