ስፓርት

ከ4ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉት የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደረገባቸው

By Mikias Ayele

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ4ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ባሉ መርሐ-ግብሮች የኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሳምንት መርሐ-ግብሮች በድሬዳዋ ስታዲየም ከተደረጉ በኋላ በብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከውድድሩ መሰረዙን ተከትሎም በ18 ተሳታፊ ክለቦች የሚካሄደው ሊግ÷ ከ4ኛ ሳምንት በኋላ ያለው መርሐ-ግብር ማስተካከያ ተደርጎበታል መባሉን የማኅበሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም መሰረት ከ5ኛ ሳምንት ውጭ ጠዋት 3 ሰዓት ከ30 ላይ የሚደረግ ጨዋታ እንደማይኖር ነው ሪሚየር ሊጉ ያስታወቀው፡፡

በተመሳሳይ ከ5ኛ ሳምንት ውጭ ባሉ የቀሪ ሳምንታት መርሐ-ግብሮች ላይ ሁለት አራፊ ቡድኖች በየሳምንቱ እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡