የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም የእይታ ቀን ተከበረ

By amele Demisew

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የዓለም የእይታ ቀን “ትኩረት ለልጆች ዐይን ጤና” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

ቀኑ በልጆች የዐይን ጤና ላይ ትኩረት በማድረግ በምርመራ፣ በዐይን ቀዶ ህክምናና የዐይን ጤና ስትራቴጂን ይፋ በማድረግ ተከብሯል።

የጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን በወቅቱ÷ በርካታ ሕፃናት መከላከል በሚቻሉ የዐይን ጤና ችግሮች ምክንያት እይታቸውን እንደሚያጡ ገልጸዋል፡፡

ወላጆችና አሳዳጊዎች በተለይም እየተለመደ የመጣውን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አጠቃቀም ለዐይን ጤና ችግር እንደሚዳርግ ተገንዝበው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ማመልከታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡