Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ እየተሰጠ ያለው የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ለ2 ቀናት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማው በዘመቻ እየተሰጠ ያለውን የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ለተጨማሪ ሁለት ቀናት መራዘሙን አስታወቀ፡፡

የክትባት ዘመቻው በአዲስ አበባ ከመስከረም 27 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት እየተሰጠ ቆይቷል።

ሆኖም በከተማ አስተዳደሩ ክትባቱን ማግኘት ያለባቸው ሁሉንም ህጻናት ለማዳረስ በማለም ለሁለት ቀናት በማራዘም ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ.ም ክትባቱ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በዚህም ወላጆች እና አሳዳጊዎች እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን በእነዚህ ቀናት በማስከተብ ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ መልዕክት መተላለፉን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version