ቴክ

ኤሎን መስክ ሳይበርካብ የተባለውን አዲሱን መኪና ይፋ አደረገ

By Mikias Ayele

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴስላ እና ኤክስ ኩባንያ ባለቤቱ ኤሎን መስክ ሲጠበቅ የነበረውን ‘ሳይበርካብ’ የተባለውን አዲስ መኪና ይፋ አድርጓል።

እጅግ ዘመናዊ የተባለው ይህ አዲሱ መኪና ባለ ሁለት በር ሆኖ ያለ አሽከርካሪ ሊንቀሳቀስ የሚችል መሆኑ ተነግሯል።

የኩባንያው ባለቤት ኤሎን መስክ÷ በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሰዎች ከሚንቀሳቀሱት ተሽከርካሪዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአዲሱ ተሽከርካሪ ባለቤቶች መኪናውን መንዳት ሳይጠበቅባቸው መኪናው በራሱ ተንቀሳቅሶ በመስራት ለባለቤቶቹ ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል አስገንዝቧል፡፡

የመኪናውን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ እና ዋጋችው ተመጣጣን የሆኑ ካሜራዎች የተገጠሙለት ሲሆን ቴስላ ኩባንያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም መኪናዎችን ለማንቀሳቀስ ማቀዱም ተመላክቷል፡፡

መኪናው ከፈረንጆቹ 2027 አስቀድሞ ገበያ ላይ መዋል እንደሚጀምር የገለጸው ኤሎን መስክ፤ በ30 ሺህ ዶላር ወይም 23 ሺህ ፓውንድ ለገበያ እንደሚቀርብ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡