Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ፑቲን ለፕሬዚዳንት ታዬ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲስ ለተሰየሙት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በተመሳሳይ የሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሻንሙጋራትናም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በመሰየማቸው ‘የእንኳን ደስ አለዎት’ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ፕሬዚዳንት ታዬ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

Exit mobile version