የሀገር ውስጥ ዜና

የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት ስራ ተጀመረ

By amele Demisew

October 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎትን በይፋ ጀምረዋል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በይፉ አገልግሎት መጀመራቸው ተገልጿል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረትእንደገለጹት÷ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ሆነው ቆይተዋል።

ቀደም ሲል እየተከናወነ የቆየው ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት የመስጠት ተግባር በአዲሱ በጀት አመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡