የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ዴንማርክ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

By Melaku Gedif

October 10, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ አዲስ ከተሾሙት የዴንማርክ አምባሳደር ሱን ክሮግስትረፕ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በልማት ትብብር ፣ አየር ንብረት ለውጥን በመከላከልና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ዘርፍ አጋርነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማስፋፋት መስማማታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሱን ክሮግስትረፕ በበኩላቸው÷ ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የልማት ድጋፍ አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።