Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቱቱ መላኩ የቢቢሲ የልዩነት ፈጣሪዎች ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቱቱ መላኩ የቢቢሲ የልዩነት ፈጣሪዎች ሽልማትን አሸንፋለች፡፡

ቱቱ መላኩ በምትኖርበት ከተማ ማህበረሰብ ውስጥ ልዩነት የሚፈጥር ሥራ አከናውናለች በሚል ነው ቢቢሲ ሬዲዮ ቤርክሻየር ሽልማቱን ያበረከተላት፡፡

ቢቢሲ ሬዲዮ ቤርክሻየር የልዩነት ፈጣሪዎች ሽልማት በ8 ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን÷ ይህም በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ልዩነት የሚፈጥር ሥራ ያከናወኑ ሰዎች ሥራዎች በዳኞች ከተገመገሙ በኋላ የሚሰጥ ሽልማት ነው።

ቱቱን ጨምሮ ለሚኖሩበት ማህበረሰብ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የማህበረሰብ ጀግኖች በሬዲንግ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሽልማታቸውን መቀበላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቱቱ በምትኖርበት ከተማ ታዋቂ የሆነ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት (ካፌ) ባለቤት ስትሆን÷ ሽልማቱን ያገኘችው ከስራዋ ጋር ተያይዞ ለማህበረሰቡ ባበረከተችው በጎ አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።

Exit mobile version