አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ሰኞ ማምሻውን ህይወቱ አለፈ።
አርቲስቱ ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ገላን ኮንዲሚኒየም አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለኢቢሲ እንደተናሩት፥ የከተማዋ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ግድያውን በፈፀም የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግልሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
በወንጀሉ ምርመራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ነው ያመለከቱት።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በከተማዋ ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ያመለከተት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ አሳስበዋል።