Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ10 ሚሊየን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የ10 ሚሊየን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ የግብርና እና የተቀናበሩ የግብርና ምርት ውጤቶች ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ስምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሃን ዲዩግ ቾ ተፈራርመዋል፡፡

ሃን ዲዩግ ቾ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ስምምነቱ የሀገራቱን ወዳጅነትን ከማጠናከሩ ባለፈ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያግዝ አንስተዋል፡፡

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ድጋፉ ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ እድገት ተስፋ ሰጪና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡

Exit mobile version