የሀገር ውስጥ ዜና

ኦቪድ ሪልስቴት ከሃይብሪድ ዲዛንስ እና ከሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

By amele Demisew

October 10, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦቪድ ሪልስቴት ከሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ከሰዋሰው ሚዲያ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የራይድ አሽከርካሪዎች እና ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የሚሰሩ አርቲስቶችን የቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የኦቪድ ሪልስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬው በየነ (ኢ/ር)ኦቪድ ሪልስቴት ሁሉንም ማህበረሰብ የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ÷ከሁለቱ ተቋማት ጋር ያደረገው ስምምነትም የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡

የሃይብሪድ ዲዛይንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሩ በበኩላቸው÷ ስምምነቱ የራይድ አሽከርካሪዎችን የቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

የሰዋሰው ቤተሰቦች ከኦቪድ ጋር በተደረገው ስምምነት የቤት ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ደግሞ የሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ ሃብቱ ነጋሽ(ኢ/ር) ናቸው፡፡

ቤቶቹ በገላን ጉራ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው እንደሚከናወን ያነሱት ፍሬው(ኢ/ር)÷ በቀጣይም ከመንግስት እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ስምምነቱ ይቀጥላል ብለዋል።

ኦቪድ ሪል ስቴት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከ70 ሺህ በላይ ቤቶችን እየገነባ መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በቅድስት ብርሃኑ