Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 ረቂቅ አዋጆችን ለቋሚ ኮሚቴዎች መራ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ እና የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

እንዲሁም የመድኃኒት ፈንድና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ረቂቅ አዋጅም ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የምክር ቤቱን 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ አጽድቋል።

 

Exit mobile version