አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሪዎች አዲስ ለተሰየሙት የኢ.ፌ.ዲ .ሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ አለዎት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መሪዎቹ ፕሬዚዳንት ታዬ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም መመኘታቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።
በተመሳሳይ የሳዑዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽና ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።