አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024” በሚል መሪ ሐሳብ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሳምንት በመጪው ሕዳር ወር ላይ እንደሚካሄድ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሳምንቱን “በዓይነቱ ልዩ በሆነ ታላቅ ዓለም አቀፍ ዐውደ-ርዕይና ሲምፖዚየም ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት አስጀምረናል” ብለዋል፡፡
በተለይም ከለውጡ ጊዜ ወዲህ መንግስት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት፣ በከተማ ትራንስፖርት እና አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡