የሀገር ውስጥ ዜና

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከብሪታኒያ የውጭ የጋራ ብልጽግናና ልማት ጽሕፈት ቤት ቋሚ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

October 09, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከብሪታኒያ የውጭ የጋራ ብልጽግናና ልማት ጽሕፈት ቤት ቋሚ ተጠሪ ኒክ ዳዬር ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱን ያደረጉት በአፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በለንደን እየተካሄደ ከሚገኘው ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ነው፡፡

በዚሁ ወቅትም ሚኒስትር ዴዔታው ኢትዮጵያ ለውጪ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች መሆኗን በማስረዳት ለአብነትም የኢኮኖሚ ሪፎረምን ጨምሮ የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ እና ሌሎች ትልልቅ ሥራዎች ማከናወኗን አብራርተዋል፡፡

በኢንቨስተመንት ዘርፍ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የኢትዮጵያን መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

የብሪታኒያ መንግሥትም ለኢትዮጵያ ዘርፈ-ብዙ ድጋፍ ማመስገናቸውን በለንድን ኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኒክ ዳዬር በበኩላቸው ኢትዮጵያ የኢንቨስተሮች ተቀዳሚ ምርጫ ለመሆን እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ በማድነቅ አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡