Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው በዛሬው ዕለት ጠዋት 4 ሰዓት አካባቢ ከጎሮ ወደ ኮዬ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተሽከሪካሪ የአውቶብስ ትኬት በመቁረጥ ላይ የነበሩ ዜጎችን በመግጨቱ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ አሽከርካሪውን ጨምሮ 7 ሰዎች ላይ ከባደና ቀላል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉት ዜጎች ሁሉም ሴቶች መሆናቸውን ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

አደጋው እጅግ አሰቃቂ መሆኑን የጠቆሙት ም/ኮማንደሩ÷ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በጤና ተቋማት ሕክምና እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version