አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡
በውይይቱም፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሁናዊ ተግባራት በተመለከተ በኮሚሽነሮች ገለጻ እና ማብራርያ ተደርጓል።
የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ሶፊ ኢመስበርግር÷ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የምክክር ሂደት አድንቀው ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የጀመሩትን የትብብር ማዕቀፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣዮቹ ጊዜያትም ኮሚሽኑ ነፃነቱን እና ገለልተኝነቱን በጠበቀ መልኩ ከአውሮፓ ህብረት ጋር እንደሚሰራ መግለፃቸውን ከምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡