Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኤሊዩድ ኪፕቾጌ በድጋሚ የዩኔስኮ የስፖርት አምባሳደር ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለት ጊዜ የኦሊፒክ ሻምፒዮኑ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የስፖርት አምባሳደር ሆኗል፡፡

ኬኒያዊው የማራቶን ባለታሪክ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ለሁለት ዓመታት ነው የስፖርት አምባሳደር በመሆን የተሰየመው፡፡

የ39 ዓመቱ አትሌት በስፖርት ዘርፍ ላሳየው ዲሲፕሊን እና ታማኝነት እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ እና በህፃናት ትምህርት ዘርፍ ባበረከተው አስተዋፅኦ ምክንያት ለአምባሳደርነት መመረጡ ተመላክቷል፡፡

ኪፕቾጌ ከስፖርቱ ጎን ለጎን ፋውንዴሽን በማቋቋም በህፃናት ትምህርት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፆ፤ በዩኔስኮ የተጣለበትን የአምባሳደርነት ሃላፊነቱን ለመወጣት ጥረት እንደሚያደርግ ማረጋገጡን ፐልስ ስፖርት ዘግቧል፡፡

Exit mobile version