አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዮርዳኖስ ዋና ከተማ አማን ተጨማሪ ሶስት በረራዎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
በረራቹ በየሳምቱ ሰኞ፣ ረቡዕ እና ዓርብ ቀናት የሚከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል፡፡
ይህን ተከትሎም አየር መንገዱ ወደ አማን ከተማ የሚያደርገው ሳምታዊ በረራ ወደ 10 ከፍ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡