Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ ‘ሃሪኬን ሚልተን’ እየተመታች ያለችው ፍሎሪዳ ነዋሪዎች ከቀያቸው እየወጡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካዋ ግዛት ፍሎሪዳ የተከሰተው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ (ሃሪኬን ሚልተን) በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስገደዱ ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከተከሰተው በይበልጥ በቀጣዮቹ ቀናት ፍሎሪዳ ዝናብ በቀላቀለ አውሎ ነፋስ ልትመታ እንደመትችል እና በዚህም 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች በአደጋው ሊጎዱ ስለሚችሉ ከአካባቢው እንዲወጡ አዝዘዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው እና በቀጣይም በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

በፍሎሪዳ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ቀደም ብለው መዘጋታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሰሞኑን በጆርጂያ፣ ፍሎሪዳ፣ ደቡብ ካሮላይና፣ ቴነሲ፣ ቨርጂኒያ እና ሰሜን ካሮላይና የተከሰተው ‘ሄለን ሃሪ ኬን’ የ225 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡

Exit mobile version