ስፓርት

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ

By Mikias Ayele

October 09, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው አማካይ ኮል ፓልመር የ2023/24 የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡

የ22 ዓመቱ ፓልመር በሕዝብ በተደረገ ምርጫ የሪያል ማድሪዱን ጁድ ቤሊንግሃም እና የአርሰናሉን ቡካዮ ሳካን በድምፅ በመብለጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡

ፓልመር ለሦስቱ አናብስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው ባለፈው ሕዳር ወር እንግሊዝ ማልታን 2 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሲሆን÷ ዩሮ 2024ትን ጨምሮ ለሀገሩ ዘጠኝ ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

ኮል ፓልመር ባለፈው ነሐሴ ወር የታዋቂ እግር ኳስ ተጨዋቾች ማኅበር (ፒ ኤፍ ኤ) የዓመቱ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን እንዲሁም የቼልሲ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡