Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን አየር መንገዶች በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዘርባጃን አየር መንገድ (AZAL) ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡

ሁለቱ አየር መንገዶች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን የአዘርባጃን አየርመንገድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው ጽሁፍ አስታውቋል፡፡

የትብብር ስምምነቱ ለአየር መንገዶቹ ደንበኞች ተጨማሪ የጉዞ መስመሮችን እንዲጠቀሙ የሚያደርግና አለም አቀፍ የጉዞ እድሎችን የሚያሰፋ መሆኑንም አየር መንገዱ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆንላቸው መልካም እድል እንደሚፈጥርም ገልጿል፡፡

“በአለምአቀፍ ደረጃ ብሎም በአፍሪካ ትልቅ ስም ካለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መስራታችን የአየር መንገዳችንን አለምአቀፍ ተሳትፎ ይበልጥ ያጠነክራል “ሲልም የአዘርባጅን አየር መንገድ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

Exit mobile version