አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሩህ ኢትዮጵያ የሴቶች የፈጠራ ሐሳብ ውድድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።
“ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘውን ውድድር የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
በውድድሩ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰለሞን ሶካ÷ ሴቶች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ያላቸውን ክኅሎት ለማዳበር በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩም ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የፈጠራ ሐሳብ ያላቸውን ሴቶች በማወዳደር እያበቃ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ዛሬ በተጀመረው ውድድርም ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ 70 ሴቶች እንደሚሳተፉ እና ለ10 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚበረከት ተመላክቷል፡፡