የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያና ቻይናን ግንኙነት በይበልጥ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ

By amele Demisew

October 08, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ቻይናን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በይበልጥ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼን ሃይ ጋር በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አምባሳደር ምሥጋኑ አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ቻይና ብሪክስን ጨምሮ በሌሎች የባለብዙ ወገን መድረኮች ማዕቀፍ ውስጥ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይም ምክክር አድርገዋል፡፡