የሀገር ውስጥ ዜና

የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By ዮሐንስ ደርበው

October 08, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው ብለዋል።

በያዝነው የምርት ዘመንም የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

34 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ፍራፍሬ እና 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል አትክልት መመረቱንም አስረድተዋል፡፡

ይህን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት በትጋት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም የጋራ እድገት ለማስገኘት ብሎም የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መሥራት ይገባል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡