ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By ዮሐንስ ደርበው

October 08, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ዋና ጸሐፊው በመልዕክታቸው ÷ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያን ጥቅም በማስጠበቅና ቀጣናዊ ትብብር እንዲሻሻል ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

አሁን ከተሰየሙት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ኢጋድ በጋራ ጉዳዮች ላይ በጥሩ የትብብር መንፈስ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም አረጋግጠዋል።

በተለይም ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር፣ በሰላምና በልማት መስኮች በትብብር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የኢጋድ መረጃ አመላክቷል።