የሀገር ውስጥ ዜና

የባሕርዳር ከተማን የኮሪደር ልማት በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

By Melaku Gedif

October 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕርዳር ኮሪደር ልማት ሥራ በተቀመጠለት ጥራትና ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ጎሹ እንዳላመው አስታወቁ፡፡

ከንቲባ ጎሹ እና ሌሎች የባሕርዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የከተማዋን የኮሪደር ልማት ሥራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ከንቲባ ጎሹ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የባሕርዳር ኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋ የደረሰችበትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው ጥራቱን ጠብቆ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡፡