የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

By Mikias Ayele

October 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የጦር ሃይሎች ም/ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና የአማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ተሳትፈዋል፡፡

የሥራ ሃላፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኙትን ካርቪኮ ኢትዮጵያ እና ትራይባስ ኢትዮጵያ የሚያመርቷቸውን ምርቶች ተዘዋውረው መመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል