የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ለፕሬዚዳንት ታዬ  የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Mikias Ayele

October 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ ለተሰየሙት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ም/ጠ/ሚ ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ፕሬዚዳንት ታዬ በዚህ ትልቅ የሃላፊነት ቦታ ኢትዮጵያን በቅንነት፣ በጥበብና በጥልቅ የዓላማ ስሜት እንደሚያገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የአገልግሎት ዘመናቸው ስኬታማ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት  ሣሕለ ወርቅ  ዘውዴ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡