Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሙሳ ፋኪ መሃማት ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ  የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት አዲስ ለተሰየሙት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው ÷ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ አዲስ የተሰየሙት ፕሬዚዳንት ታዬ እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፉት ስድስት ዓመታት በነበራቸው ሃላፊነት ለሰጡት ታሪካዊ እና በሳል አመራር ሊቀመንበሩ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን በምታደርገው ጥረት የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ማድረጉን እደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version