በቅርቡ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚክ ማሻሻያ ማስቀጠልና ሁሉን አቀፍ ለውጥ ማምጣት፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይገበር ኢኮኖሚ ለመገንባት ይሰራል፤ የሀገሪቱ አጠቃላይ እድገት 8 ነጥብ 4 በመቶ ለማድረግ ይሰራል፣
የታክስ ማሻሻያ ላይ በመሰራት፣ የመንግስትን አሰራር በማዘመን፣ ማበረታትና ድጎማዎችን በማድረግ የሀገር ውስጥ ገቢን 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ለማድረስ ይሰራል፣
በግጭት የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ ይሰራል፣
በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻው ሊጎዱ ለሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጎማ በማድረግ የኢኮኖሚ ማሻሻው ውጤታማ እንዲሆን ይሰራል፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ይሰራል፣
ምርቶችን እሴት ጨምሮ በመላክ ውጤታማነታቸውን በማሻሻል ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ይሰራል፣ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ገቢን ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማድረስ ይሰራል
አስቻይ የሆኑ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችን በመቅረጽ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፣ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን የስራ እድል ለመፍጠር ይሰራል፣
ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ይሰራል፤ ብሄራዊ ጥቅማችን በማስጠበቅ ከሀገራት ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን፤ አዳዲስ ስትራቴጂካዊ አጋር ሀገራትን ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል፤
ከጸጥታ ስጋት እና ከሌብነት ጋር በተያያዘ የነበሩ ችግሮችን ሙሉሙሉ በአንዴ መቅረፍ ባይቻልም ለመቀነስ ይሰራል።
በአመለወርቅ ደምሰው