Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ በበጀት ዓመቱ ለ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 በጀት ዓመት ለ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በ2107 ዓ.ም በመንግሥት የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ተመራጭ እንድትሆን ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም በዘርፉ አስቻይ የሆኑ አሰራሮችን በመተግበር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሀገራት አንዷ ሆና እንድትቀጥል ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል በመፍጠር ረገድ በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቅሰው÷ በዓመቱ ለ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 700 ሺህ የሚሆነው የውጭ ሀገራት የሥራ እድል መሆኑን ነው ፕሬዚዳንቱ ያስረዱት፡፡

በዲፕሎማሲ ረገድ ከጎረቤ ሀገራት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በማጠናከርና ሀገራዊ ጥቅሞችን በማሳደግ በሰላም፣ በጸጥታ፣ በኢኮኖሚና በቀጣናዊ ትስስር የጋራ ጥቅምን በሚስገኙ ሥራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version