አሁን ላይ ጋን በጠጠር ይደገፋል የሚለውን ነባራዊ ሀገራዊ ብሂል፤ ጠጠር በጋን ይደገፋል ወደሚል ትርጉመ ቢስ አባባል የቀየርነው ይመስላል፡፡ መንግሥታችን በአንድ በኩል ይሕንን ለማረቅ በሌላ በኩል ከዚህ ሐሳብ በእጅጉ የራቀ ትውልድ ለመቅረጽ በመሥራት ላይ ይገኛል፣
ጥልቅ ማስተዋል፣ ማሰላሰል፣ አርቆ ማሰብና ትዕግስት የኢትዮጵያ የጽናት ዋልታዎች ናቸው፣
አሠናካይ ሐሳቦችን በማራቅ ወደፊት መራመድ ያስፈልጋል፣
ባለፉት ሦስት ዓመታት የፋይናንሱ ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡ በዚህም የሁሉም ባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ 2 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ደርሷል፣
በ2016 ዓ.ም አጠቃላይ የብድር አሰጣጥ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ዘርፎች እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በተለይም ለግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የሚሰጠው ብድር አድጓል፣
በተጨማሪም አካታች የፋይናንስ ዘርፍን በማጎልበት ከ461 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ተሠራጭቷል፣
የሞባይል ዋሌት ተጠቃሚዎች መጠን በ2014 ከነበረበት 43 ነጥብ 2 ሚሊየን 2015 ላይ ወደ 68 ነጥብ 6 ሚሊየን አድጓል፡፡ በ2016 ደግሞ 107 ነጥብ 5 ሚሊየን ማሳደግ ተችሏል፡፡
በዮሐንስ ደርበው