የሀገር ውስጥ ዜና

በአፋር ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ የፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ ነው

By Melaku Gedif

October 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) በሽታ የመከላከያ ክትባት መሰጠት ጀምሯል፡፡

የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት እደሚሰጥ ነው የተመላከተው፡፡

በአፋር ክልል በክትባት ዘመቻው ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ364 ሺህ በላይ ሕጻናት እንደሚከተቡ ተጠቁሟል፡፡

የክልሉና ከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮዎች የክትባት መርሐ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርገው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡