Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከሠራዊቱ ጋር በቅንጅት በመሠራቱ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ሥራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
በክልሉ እና አጎራባች አካባቢዎች የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ በተካሄደ መድረክ ላይ አቶ አሻድሊ÷ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተፈጥረው የነበሩ ችግሮችን ለማስተካከል በተከናወነ ሥራ ሠራዊቱ አካባቢው እንዲረጋጋ ማድረጉን ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የሰላምና ፀጥታ ውይይት በማድረግ ችግሮችን ማስተካከል ተችሏል ማለታቸውን ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ክልሉ እንደታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሚገኝበት በመሆኑ በቀጣናው የሚከናወን የልማት ሥራ በውጭና በውስጥ ጠላቶች እንዳይደናቀፍ በተሠራው ሥራ ውጤት መመዝገቡንም ገልጸዋል፡፡
የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሜጄር ጀኔራል ሙላት ጀልዱ በበኩላቸው÷ ሕዝቡ ሰላሙ ተጠብቆ በሀገሪቱ በሚከናወኑ ልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆን በቀጣናው የሚንቀሳቀሱ የሸኔ ሽብር ቡድንና ፅንፈኛውን ኃይል በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
Exit mobile version