Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፍሮንቲየር አየር መንገድ አውሮፕላን በማረፍ ላይ ሳለ በእሳት የተያያዘበትን መንስዔ እያጣራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ንብረትነቱ የፍሮንቲየር አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን ቅዳሜ አመሻሽ ላይ ከሳንዲያጎ ወደ ላስቬጋስ ሲበር በማረፍ ላይ ሳለ በእሳት የተያያዘበትን መንስዔ እያጣራ መሆኑ ተገለጸ።

190 መንገዶኞችን እና ሰባት የበረራ አባላትን ይዞ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላኑ፤ በሃሪ ሬድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሊያርፍ ሲል ጎማው አካባቢ ጭስ እና የእሳት ነበልባል ታይቷል።

በዚህም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ እሳቱን ማጥፋትና መንገደኞችን ያለምንም ጉዳት ማስወጣት መቻሉን ኩባንያው በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡

የአደጋው መንስዔ በምርመራ ላይ እንዳለ የሀሪ ሬይድ አለም አቀፍ አየር መንገድ መጠቆሙን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ የብሄራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የአደጋው መንስዔን የማጣራት ስራ በትናንትናው እለት በይፋ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

Exit mobile version